ይህ መተግበሪያ ለGoogle የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ አቋራጭ ያቀርባል፣ ይህም የይለፍ ቃል፣ የይለፍ ቁልፎች እና ሌሎችን ለማግኘት እና ለማስተዳደር ይበልጥ ፈጣን እና ቀላል ያደርገዋል።
Google የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ ቀድሞውኑ Android ስልክዎ ውስጥ የተገነባ ነው፣ ይህም ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ የይለፍ ቃላትዎን ያስቀምጣል እና በፍጥነት እንዲገቡ ያግዛል።
የይለፍ ቃላት ጥረት የማይጠይቁ ተድርገው፦
የይለፍ ቃላትን ማስታወስ ወይም ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል ሳያስፈልግዎት ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ውስጥ በማንኛውም መሣሪያ ይግቡ። Google የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ Chrome (በሁሉም መሠረተ ሥርዓቶች) እና Android ውስጥ የተሰራ ነው።